Social

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

ከመላው ሃገሪቱ የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል ፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ ለወጣቱ ትውልድ ሃገራዊ እሴቶችን በማውረስ ዘመናዊነትን በጥበብ እና በብልሃት እንዲላበስ፥ የሃገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል አሳስበዋል።

ሚኒስትሯ የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ከማስፈንና ከማረጋገጥ አንጻር እስካሁን ላከናወኑት ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ተንከባካቢ ቢሆኑም በሃገር ሽማግሌዎች ስም የሚነግዱና ሰላም ከሚያውኩ አካላት ጋር የሚሰሩ በመኖራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባልም ብለዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami