ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው አነጋገሩ።
ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን ተቀብለው ማነጋገራቸው ተሰምቷል።
በህዳር ወር ኢትዮጵያን የጎበኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ጋር የተደረገው ውይይት ቀጣይ የሆነው የዛሬው ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር በማጥናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ::