Politics

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ እርሳቸውን ተክተው ከተሾሙት በመንግታቱ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ ጋር መከሩ

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ እርሳቸውን ተክተው ከተሾሙት በመንግታቱ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ ጋር መከሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት የአፍሪካ ህብረት ልዩ  ተወካይ ሆነው የተሾሙትን ሀና ሰርዋ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ልዩ ተወካይዋ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን በመተካት የተሾሙ ሲሆን የጉብኝታቸው ዓላማም ለፕሬዝዳንቷ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ለማስተላለፍና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ፕሬዝዳንቷ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቢሮና በሌሎች ኃላፊነቶች ላይ የነበራቸውን የመሪነት ሚና “በጣም ጥሩ” እንደነበር ተነግረዋል።

በቀጣይም የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጋር የሚሰራቸውን ስራዎች የተሻለ ለማድረግ በመመካከር እንሰራለን ነው ያሉት።

የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይዋ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ ነው በማለትም አድንቆታቸውን ገልፀዋል ፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅም በኢትዮጵያ ታሪክ ሴቶች ወደ መሪነት ቦታ እንዲመጡ  እድል መፈጠሩንና ይህም ለሌሎች አገራት እንደአብነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል ።

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami