Social

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም ይሁን የግጭት ፍላጎትም  የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

በአማራና ትግራይ ህዝቦች መካከል ግጭትም ይሁን የግጭት ፍላጎትም  የለም አሉ የሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች

ርዕሳነ መስተዳደሮቹ ይህንን ያሉት የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አከባቢዎች ሲያደርጉት በነበረውን የሰላም ጉዞ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ተገኝተው ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ አካባቢዎች የሰላም አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀሳቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

የአማራ ህዝብ እና የትግራይ ህዝብ የጋራ ታሪክ እና እሴት ያለው ህዘብ ነው ያሉት  አቶ ገዱ አንዱ አንዱን የሚፈራ ሳይሆን አንዱ በአንዱ የሚኮራ ህዝብ ነው ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ እሴት እየተሸረሸረ መምጣቱንም ርእሰ መስተዳድሩ አልሸሸጉም።

የአማራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ግጭት አይፈልግም፤ ይልቁንም በመካከላቸው ያለው አለመግባባት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና በውይይት እንዲፈታ ይፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

የአማራ ህዝብ መሪ እንደመሆኔ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ በቁርጠኝነት እሰራለሁ ሲሉም አረጋግጠዋል ።

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በበኩላቸው፥ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ሰላምን ለማምጣት ላደረጉት ጥረት ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ለተፈጠሩ ችግሮች የእከሌ ነው የሚባል ነገር የለም ያሉት ዶክተር ደብረጺዮን፥ ሁላችንም አጥፍተናል፤ ይህንን ለማስተካከልም መረባረብ አለብን ነው ያሉት ።

ከሰላም በላይ ምንም ነገር የለም ያሉት ዶክተር ደብረጺዮን፥ የፖለቲካን ጉዳይ ለብቻ የሰላምን ጉዳይ ለብቻ አድርገን መስራት አለብን ሲሉም ተናግረዋል።

የፖለቲካውን ጉዳይ ለምርጫ በመተው ሁላችንም በሰላሙ ጉዳይ መረባረብ ይገባናል ነው ያሉት ዶክተር ደብረጺዮን ።ዜናው የኤፍቢሲ ነው።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami