Uncategorized

የአሜሪካ ፖሊስ ለኢራን ቲሌቭዥን የምትሰራዋን ጋዜጠኛ አስሯታል

የአሜሪካ ፖሊስ ለኢራን ቲሌቭዥን የምትሰራዋን ጋዜጠኛ አስሯታል

ሮይተርስ ፕሬስ ቴሌቭዥንን ጠቅሶ እንደዘገበው ባልታወቀ ምክንያት የአሜሪካ ፖሊስ ጋዜጠኛዋን ሴይንት ሉዊስ በሚገኘው ላምበርት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው በቁጥጥር ስር ያዋላት፡፡

በትውልድ አሜሪካዊት በዜግነት ደግሞ ኢራናዊት የሆነቸው ማርዜይ ሀሺሚ በኢራን መንግስት ለሚተዳደረው ፕሬስ ቴሌቭዥን መስራት ከጀመረች ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡

ሀሺሚ ወደ አሜሪካ ያቀናቸው የታመመ ወንድሟን ለመጠየቅ እንደነበር እና ከተያዘች በኋላ የኤፍ ቢ አይ ሰዎች ወደ ዋሽንግተን እስር ቤት እንዳዛወሯት  አስታውቋል፡፡

የአሜሪካው ማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ ኤፍ ቢ አይ ግን  እስካሁን ጋዜጠኛዋ ስለታሰረችበት ጉዳይ ምንም ዓይት አስተያየት አልሰጠም ተብሏል፡፡

ሮይተርስ በዘገባው ምንም እንኳን ወሬውን ከታማኝ ምንጭ እንዳገኘው ባያረጋግጥም ሀሺሚ በእስር ቤት ሂጃብ እንዳትለብስ ተከልክላለች፤ የሚቀርብላት ምግብም ለመመገብ ሀይማኖቷ የሚፈቅድላት  አይደለም ሲል አስነብቧል፡፡

ፕሬስ ቴሌቭዥን ደግሞ ታሳሪዋ ከሴት ልጇ በስተቀር ወዳጅ ዘመዶቿ ጋር እንዳትገናኝ ክልከላ እንደተደረገባት የሚያስረዳ ዘገባ አሰራጭቷል ፡፡

በቀድሞ ስሟ ሜላኒን ፍራንክሊን በመባል ትታወቅ የነበረችው ከአፍሪካ አሜሪካዊያን ቤተሰቦች የተወለደችው ጋዜጠኛዋ ስሟን የቀየረችው  የእስልምና ሀይማኖትን ከተቀበለች ወዲህ ነው፡፡

አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ አፍሪካውያን፣ ሴቶች እና ሙስሊሞች አድልዎ እንደሚደርስባቸው የሚያሳዩ  ዘገባዎችን ማቅረብው የምትታወቀው ሀሺሚ  ከተያዘች ቀናት ቢቆጠሩም እስካሁን ክስ አልተመሰረተባትም ተብሏል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami