Africa

የሊቢያ ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን አፈረሱ።

የሊቢያ ተዋጊ ሀይሎች የተኩስ አቁም ስምምነታቸውን አፈረሱ

በሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በተቀናቃኝ ሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት አምስት ሰዎች ሲገደሉ 20 የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡

ሬውተርስ የሀገሪቱን የጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው በተፋላሚ ሀይሎቹ መካከልአራት ወራት በፊት የተፈረመው  ተኩስ አቁም በከተማዋ አንፃራዊ ሰላም አስገኝቶ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት 7ኛው ብርጌድ ወይም ካኒያት ተብለው በሚጠሩት እና ትሪፖሊ ፕሮቴክሽን ፎርስ በሚባሉት ሀይሎች መካከል ዳግም ግጭቱ አገርሽቷል ነው የተባለው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ልዩ ልኡክ ቢሮ በሰጠው መግለጫ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለመጣስ የተነሳሳ ማንኛውም ወገን ሀላፊነቱን ይወስዳል ብሏል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ደርጅት  ድጋፍ ስልጣን የያዘው እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እውቅና ያለው  የሊቢያ መንግስት፤ ተኩስ አቁሙ ከተፈረመ ጀምሮ አዲስ የፀጥታና ደህንነት እቅድ  አውጥቶ እየሰራ ባለበት ወቅት ነው ግጭቱ የተጀመረው፡፡

 

 

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami