Social

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ያደረገውን ዝግጅት አጠናቅቆ ከዛሬው ከተራ በዓል ጀምሮ ወደ ስራ ገብቷል።

ፖሊስ ኮሚሽኑ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ፣ ከሌሎች የፀጥታ እና የፍትህ አካላት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በጋራ ስራ መጀመሩንም አስታውቋል።

በዓላቱ በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ለወንጀል እና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባር ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ የሰው ኃይል ማሰማራቱን ገልጿል።

በታቦት ማደሪያ ስፍራዎች በተለይም በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት ጃን ሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ተከፍተው አግልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው ነው የተገለፀው።

በጥምቀት በዓል ጸበል በሚረጭበት ወቅት  በሚፈጠር ግፊያ ምዕመናኑ ጉዳት እንዳይደርስባቸው፣ ንብረቶች እንዳይሰረቁና በማንኛውም እንቅስቃሴ ወቅት የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም ፖሊስ መክሯል።

የእምነቱ ተከታዮች በተለይ ወጣቶች ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት ሁሉ በተደራጀ መንገድ ከፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ለበዓሉ በሰላም መከበር እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ እስከበዓሉ ፍጻሜ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ፖሊስ ጠይቋል።

ህብረተሰቡ በማንኛውም ወቅት ከፀጥታ ስራ ጋር ተያያዠ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለከት እና ማንኛውንም  የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ሲፈልግ በስልክ ቁጥር 0111-26-43-77 ፣ 0111-26-43-59 ፣ 0118-27-41-51 በመደወል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃን ሜዳ ዙሪያ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑንና አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ የማቆሚያ ስፍራዎችን እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami