በጉጉት የተጠበቀውን የለንደን ደርቢ ጨዋታ አርሰናል ሲያሸንፍ፤ ሊቨርፑል መሪነቱን አስቀጥሏል
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ23ኛ ሳምንት መርሀግብር ጨዋታዎች በለንደን ደርቢ አርሰናል በኤምሬትስ ቼልሲን አስተናግዶ 2 ለ 0 ረትቷል::
አሌክሳንደር ላካዜት እና ሎረን ኮሽለኒ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል ።
የጋለ ፉክክር በነበረው ጨዋታ ቀን ላይ ወልቭስ ሌስተርን 4 ለ 3 አሸንፏል ::
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል አንፊልድ ላይ ክሪስታል ፖላስን ከመመራት ተነስቶ 4 ለ 3 አሸንፏል ። ለቀያዮቹ መሀመድ ሳላህ 2x፣ ሮቤርቶ ፊርሚኖ እና ሳዲዮ ማኔ ኳስን ከመረብ አገናኝተዋል::የኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ማንችስተር ዩናይትድ በፖግባ እና ራሽፎርድ ጎሎች ብራይተነፈንን 2 ለ 1 አሸንፏል ።
በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስትል ካርዲፍን 3 ለ 0፤ በረንማውዝ 2 ለ 0 ዌስትሀም ፤ዋትፎርድ ከበርንሊ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።
ዛሬ ቀን 10:30 ሀደርስፊልድ ታውን ከማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ምሽት 1፡30 ፉልሀም ከቶተንሀም ይጫወታሉ ።
ሊጉን ሊቨርፑልበ60 ነጥብ ይመራል ፤ ማ.ሲቲ በ53 ሁለተኛ፤ ቶተንሀም በ48 ሶስተኛ፤ ቼልሲ በ47 ነጥብ አራተኛ እንዲሁም አርሰናል እና ማ.ዩናይትድ በ44 ነጥብ አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።