EthiopiaSocial

ህጻኑ እንደተወለደ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ነጻ የትምህርት እድል አገኘ፡፡

ህጻኑ እንደተወለደ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ነጻ የትምህርት እድል አገኘ፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ የመጀመሪያዉ ህጻን መወለዱን ዩኒቨርስቲዉ አስታዉቋል፡፡

ህጻኑም  ስሙን በሁስፒታሉ ስም በማድረግ ጊዮን ተብሏል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እናት እና ልጅን ለመጠየቅ በስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ በተገኙበት ወቅት እንደተናገሩት ህፃኑ በሆስፒታሉ በመወለዱ እድሜው ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት በሚደርስበት ጊዜ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የነፃ የትምህርት እድል እንደሚያገኝ ቃል ገብተውለታል፡፡

ለህጻን ጊዮን ደመቀ ዘመኑ የደስታና የፍቅር እንዲሆንለት የመልካም ምኞት የሚያበስር ፌርማቸው ያረፈበት ካርድ ፕሬዚደንቱ ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በስጦታ አበርክተውለታል፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህጸናት ማቆያ ኃላፊ ሲስተር ኤደን አምሳሉ በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው ስም ለህጻኑ እናት ለወ/ሮ ፀሃይነሽ ዘመን የባህል አልባሳት ያበረከቱላቸው ሲሆን ህጻን ጊዮን ደመቀም በዩኒቨርሲቲው የህጻናት ማቆያ ተጠቃሚ እንደሚሆን ቃል ገብተዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami