አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ የፀረ ሚሳኤል ሲስተም ሙከራ አካሄዱ፡፡
ሁለቱ ሀገራት በጋራ ያደረጉት አዲስ የፀረ ሚሳኤል ሲስተም ሙከራ ለኢራን አንዳች መልእክት ለማስተላለፍ የታለመ ነው ተብሏል፡፡ታይምስ ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው ይህ የተሳካ ሙከራ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ካለባት ስጋት ራሷን ለመከላከል ትልቅ በራስ መተማመን ይፈጥርላታል ፡፡
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የሀገሪቱ የረጂም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎች ጥቃት ቢቃጡባት ማክሸፍ የሚያስችል ሙከራ ማድረጋችን ለጠላቶቻችን የማስጠንቀቂያ ደወል ነው ብሏል፡፡
ዘ ጀሩሳሌም ፖስት የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ ደግሞ የአሁኑ የቴል አቪቭ እንቅስቃሴ በሶሪያ የሚገኙ የኢራን ጦር ሰፈሮች ላይ ከምትሰነዝረው ጥቃት ጋር ተያይዞ ውጥረቱን እንደሚያባበስው ጥርጥር የለውም ሲል በዘገባው አስነብቧል፡፡
የእስራኤል ወታደራዊ ባለ ስልጣናት ምንም እንኳን በሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት ጣልቃ የመግባት ፖሊሲም ፍላጎትም ባይኖረንም የኢራን ወታራዊ ሀይሎች ላይ የምናደርገውን ጥቃት የሶሪያ ጦር ሀይል ለማደናቀፍ እንዳይሞክር ለማስጠንቀቅ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ኢራን በሶሪያ የምታካሂደውን የእጅ አዙር ጦርነት አንድታቆም እስራኤል በተደጋጋሚ ብታስጠነቅቅም ከወደ ቴህራን የሚሰጠው መልስ ግን ማን መንን ያዛል የሚል ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ አሁን በሶሪያ ድንበር አካባቢ የጀመሩትን የአየር ድብደባ አጠናክረው አንደሚቀጥሉበት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
እስራኤል ምንም እንኳን አጋሯ አሜሪካ ጦሯን ከሶሪያ ማስወጣት ብትጀምርም የጀመርኩትን ግዳጅ ብቻየን እወጣዋለሁ በማለት የኢራንን ጦር ከአካባቢው ጠራርጋ ለማስወጣት ቆርጣ መነሳቷን ገልፃለች፡፡
ትርጉም በመንገሻ ዓለሙ