Social

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት እንደሚደግፍ ገለጸ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት እንደሚደግፍ ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በዳቮስ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዜዳንት ፒተር ማዉረር ጋር ተወያይተዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በታየው ለውጥ ምክንያት ተስፋ መታየቱን ተናግረው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድነቀው ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የኮሚቴው ፕሬዜዳንት ፒተር ማዉረር በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ለውጥ አድንቀው፤ ኢትዮጵያ ቀጠናዊ ውህደት እንዲመሰረትና ሰላም እንዲሰፍን እየተጫወተች ላለችው ሚና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami