SportSports

በአምስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ይገናኛል

በአምስተኛ ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ይገናኛል

የኢምሬትስ ኤፍ ኤ ካፕ የአምስተኛ ዙር ጨዋታዎች የዕጣ ድልድል ትናንት ምሽት ይፋ ሁኗል፡፡

በድልድሉ በቀላሉ ወደ 16ቱ ቡድኖች የተቀላቀለው ቼልሲ ኢምሬትስ ላይ አርሰናልን ጥሎ ከመጣው የኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድን ማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡ ጨዋታው በምዕራብ ለንደኑ ስታንፎርድ ብሪጅ ይከናወናል፡፡

በፔፕ ጓርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ቀለል ያለ ተፎካካሪ የደረሰው  ሲሆን በሊግ ሁለት ከሚሳተፈው  ኒውፖርት ካውንቲ እና ሚድልስብራ አሸናፊ ጋር ይገናኛል፡፡

በአራተኛው ዙር የለንደን ተፎካካሪውን ቶተንሃም፤ በአስገራሚ ሁኔታ ድል አድርጎ ዙሩን የተዋሀደው ክሪስታል ፓላስ፤ በአምስተኛው ዙር የዕጣ ድልድል ከሊግ አንዱ ዶንካስተር ሮቨርስ የሚገጥም ይሆናል፡፡

ኢቨርተንን ጉድ የሰራው ሚልወል ከ ዊምብልደን፤  ብሪስቶል ሲቲ ከሽረውበሪና ወልቭስ አሸናፊ፤  ዋትፎርድ ከ ፖርትስማውዝና ኪው.ፒ.አር ባለድል ጋር፤ ደርቢ ካውንቲ  ከ ብራይተንና ዌስት ብሮሚች አልቢዮን አሸናፊ እንዲሁም ስዋንሲ ሲቲ ትናንት 3 ለ 3 አቻ ከተለያዩት ባርኔት አሊያም ብረንትፎርድ አላፊ ክለብ ጋር የዙሩን ፍልሚያቸውን ይከውናሉ፡፡

ጨዋታዎቹ ከየካቲት 15 እስከ 18/2019 የሚካሄዱ ሲሆን አሸናፊው ቡድን ሩብ ፍፃሜውን የሚቀላቀል ይሆናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami