የDFB pokal (የጀርመን ዋንጫ) የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬና ነገ ይካሄዳሉ
በጀርመን ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ዛሬ ምሽት አራት ያህል ግጥሚያዎች ሲከናወኑ፤ ቦርሲያ ዶርትሙንድ በሲግናል ኤዱና ፓርክ ከ ዌርደር ብሬመን ጋር ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 4፡45 ሲል ያከናውናል፡፡ ዶርትሙንድ ውድድሩን አራት ጊዜ ያህል ማሳካት የቻለ ሲሆን ብሬመን ከባየርን ሙኒክ በመቀጠል ዋንጫውን ስድስት ጊዜ ማንሳት ችሏል፡፡
የጀርመን ዋንጫን ባየርን ሙኒክ 18 ጊዜ በማሳካት ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ዲዝበርግ ከ ፓደርቦርን ይጫወታሉ፡፡
በሌሎች የምሽቱ ግጥሚያዎች ሀምቡርግ ከ ኑረምበርግ እና ሃይድንሀይም ከ ባየርን ሊቨርኩዘን ይፋለማሉ፡፡
ነገ ምሽት ደግሞ ኽርታ በርሊን ከ ባየርን ሙኒክ፣ አር.ቢ ላይፕዚህ ከ ወልፍስቡርግ፣ ሻልከ 04 ከ ፎርቱና ዱሰልዶርፍ እንዲሁም ሆልስታይል ኪል ከ ኦግስቡርግ ይጫወታሉ፡፡
የጀርመን ዋንጫ አሁን ያለውን የDFB pokal ስያሜ ከማግኘቱ በፊት፤ የቻመር ዋንጫ የሚል ስያሜን በመያዝ በ1935 ተጀመረ፤ የውድድሩ ባለቤትነት ደግሞ የጀርመን እግር ኳስ ማህበር ሲሆን ከሁለተኛው የዓለም ዋንጫ በኋላ ስያሜውን በማህበሩ መጠሪያ ቀይሯል፡፡
በውድድሩ በዋናው ቡንደስሊጋው እና በሁለተኛው የቡንደስሊጋ ውድድር የሚካፈሉ 64 ቡድኖች ይካተታሉ፡፡ የባለፈው ዓመት አሸናፊ አይንትራክት ፍራንክፉርት መሆኑ ይታወሳል፡፡