የኢሚሊያኖ ሳላ ህልፈተ ህይወት ከተሰማ በኋላ የስፖርት ቤተሰቡ ሀዘኑን እየገለፀ ነው
አርጀንቲናዊውን እግር ኳስ ተጫዋች ኢሚሊያኖ ሳላን አሳፍራ ደብዛዋ መጥፋቱ የተነገረላት ሚጢጢ አውሮፕላን በአንዳንድ በጎ ፍቃድ ለጋሾች በተሰበሰበ ገንዘብ ወድቃበታለች በተባለው ስፍራ በተደረገ አሰሳ የአውሮፕላኗ ስብርባሪ ወንዝ ውስጥ ከተገኘ በኋላ የአንድ ሰው አካል መገኘቱ ተነግሮ ነበር፡፡
ይህ የሰው አካልም ሰኞ ዕለት ከስብርባሪው ወጥቶ በቅርብ ወደ ሚገኘው የዶርሴት ፖርትላንድ ወደብ ተወስዶ በተደረገለት ምርመራ በሂሊኮፕተሯ ከነበሩት ሁለት ግለሰቦች የእግር ኳስ ተጫዋቹ ኢሚሊያኖ ሳላ መሆኑን የዶርሴ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ይሄ መረጃ ከወጣ በኋላ የስፖርት ቤተሰቡ የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ሲሆን ቤተሰቦቹንና ወዳጆቹን እያፅናና ይገኛል፡፡
ሳላ በጥር የተጫዋች የዝውውር መስኮት ከፈረንሳዩ ኖንት ወደ ዌልሱ ክለብ ካርዲፍ ሲቲ በ15 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ መዘዋወሩን ካረጋገጠና ከፈረመ በኋላ፤ የኖንት የቡድን አጋሮቹን ተሰናብቶ ጓዙን ሸክፎ ወደ አዲሱ ክለቡ እየተመለሰ በነረበት ወቅት ከቲንሿ አውሮፕላን አብራሪ ዴቪድ ኢቦትሰን ጋር መከስከሱ ይታወሳል፡፡
አርጀንቲናዊው ተጫዋች መጫወት ከሚያልምበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሳይገናኝ ህይወቱ ላትመለሰ አለፈች፡፡
የሳላ ህልፈት ቢሰማም የአብራሪው ኢቦትሰን አካል ባለመገኘቱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡
የካርዲፍ ክለብ እና ተጫዋቾች፤ የቼልሲው አንቶኒዮ ሩዲገር፣ የአርሰናሉ ሚሱት ኦዚልን ጨምሮ ሌሎች እግር ኳስ ተጫዋቾች እንዲሁም የስፖርት ቤተሰቦች የተሰማቸውን ሀዘን እየገለፁ ይገኛል፡፡