Regions

የጋምቤላ ክልል ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ሹመቶችንና አዋጆችን አጸደቀ

የጋምቤላ ክልል ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ሹመቶችንና አዋጆችን አጸደቀ፣የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ቁጥርም 21 ወደ 18 ዝቅ አድርጓል።

ለሶስት ቀናት የተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የፋይናንስ አስተዳደር ዓዋጅና የተሻሻለውን የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ ዓዋጅ አጽድቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ የዋና ኦዲትና የአስፈጻሚ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችን፥ እንዲሁም ከክልል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች የዳኞችን ሹመትም አጽድቋል፡፡

በዚሁ መሰረት አቶ ዙዋል ኛች የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ አቶ ኡቦንግ ኡጁሉ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ አቶ ኡቻላ ቻም የክልሉ ኦዲት ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ፒተር ዋው ምክትል ኃላፊ በመሆን ተሾመዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጉባዔው ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር የአስፈጻሚ አካላት ቁጥር ከነበረበት ዝቅ እንዲል የተደረገው ከበጀት አጠቃቀም፣ ከአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ተግባር አንድ መሆንና ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል በሚል ነው።

በምክር ቤቱ የተሰጠው ሹመትም የግለሰቦችን የማስፈጸም አቅምና ለሕዝቡ ቅሬታ ምላሽ መስጠትን መሠረት ያደረገ ነው ብለዋል ርዕሰመስተዳድሩ።

ከተሾሙት አመራሮች መካከል ስምንቱ አዲስ ሲሆኑ ፣ ስድስቱ በሽግሽግ የተሾሙ መሆናቸው፣ አራቱ ደግሞ ባላቸው አፈጻጸም በነበሩበት መቀጠላቸውን ነው ማወቅ የተቻለው።

አዲሱ የምክር ቤቱ ሹመትም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን የሚደግፉ አመራሮችን ወደ አስፈጻሚነት ለማምጣት ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami