Economy

˝የግብር ፍትሃዊነት  ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት˝ የተሰኘ አዲስ ጽህፈት ቤት ሊቋቋም ነው

˝የግብር ፍትሃዊነት  ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት˝ የተሰኘ አዲስ ጽህፈት ቤት ሊቋቋም ነው

ጽህፈት ቤቱ የግብር አሰባሰብ ሂደቱን የተቃና ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል

በሀገራችን  መሰብሰብ ከነበረበት ግብር ከ 80 ቢሊዩን ብር በበላዩ ሳይሰበሰብ እንደቀረ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከንግድ ስርዓት ውጭ በመሆን፤ ለመንግስት የሚገባውን  ከፍያ አለመፈጸም ፤በታክስ መረብ ውስጥ አለመታወቅ እና በአግባቡ ተመዝገበው የቲን ስርዓት ውስጥ አለመካተት  ዋንኞቹ  ችግሮች እንደሆኑ ይነገራል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና መንግስት ከታክስ ማግኘት የሚገባውን  እንዲያገኝ ለማድረግ ˝ሀገሬን እወዳለሁ ግዴታዬንም እወጣለሁ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል  ሀገራዊ ንቅናቄ እያደረገ ይገኛል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱም  የዚሁ አካል የሆነ ˝የግብር ፍትሃዊነት  ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት˝ የተሰኘ አዲስ ፅህፈት ቤት  ለመክፈት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ሰምተናል፡

የዚህን ፕሮጀክት የመግባቢያ ሰነድ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ገቢዎች ባለስልጣን  በጋራ ፈርመውታል፡፡

የፕሮጀክት ፅህፈት ቤቱ ገለልተኛ በሆኑ ምሁራን  እና ጥሩ ስነምግባር ባላቸው የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የሚዋቀር ሲሆን በዋናነት የንግድ እንቅስቃሴዎች ያሉባቸውን አካባቢዎች ቢሮውን ከፍቶ እንደሚሰራ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በ 2017 ዓ.ም  መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ለመካተት ዕቅድ ቢኖራትም  የሀገር  ውስጥ ገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ደካማ ከመሆኑ አንፃር  መንግስትን ለዕድገት ሊያወጣ የሚገባውን  ገንዘብ አሳጥቶታል ተብሏል፡፡

 

 

 

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami