Uncategorized

ለአዲስ አበባ ዋና ዋና ወንዞች የተፋሰስ ልማት የ29 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ሊደረግ ነው፡፡

ለአዲስ አበባ ዋና ዋና ወንዞች የተፋሰስ ልማት የ29 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ሊደረግ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዋና ዋና ወንዞችንና ተፋሰሶችን መሠረት ያደረገ ‹‹የአዲስ አበባ የተፋሰስ ወንዞች ዳርቻ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር›› ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት በይፋ ይጀመራል፡፡

መርሀ-ግብሩ በ29 ቢሊዮን ብር ወጭይከናወናል፤ በሦስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅም ይጠበቃል፡፡

መርሀ-ግብሩ አዲስ አበባን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረ ሆኖ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል፡፡ ባንች ይቀጡ እና ቀበና ወንዝ ተፋሰስ የመርሃ-ግብሩ የሚሸፍናቸው ተፋሰሶች ናቸው፡፡

በመርሀ-ግብሩ የሦስት ዓመታት ቆይታ 4 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ ይጠበቃል፡፡ ድልድዮች፣ ሰው ሰራሽ ሐይቆች፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ የውኃ ትራንስፖርት እና የንግድ ማዕከላትን ያካተተ ግንባታ እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami