የኢትዮ- ህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማዕከል ምስረታ በህንድ ይፋ ሆነ፡፡
በህንድ በተካሄደዉ ‹‹የሪስርችና ዲቨሎፕመንት›› ጉባኤ ላይ ተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር.ጌታሁን መኩሪያ ከህንድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የመሬት ሳይንስ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ህብረት ሚኒስትር ጋር የቴክኖሎጂ የማዕከሉን ምስረታ ይፋ አድርገዋል፡፡
የማዕከሉ ግንባታ ወጪ ሙሉ ለሙሉ በህንድ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከሉ ግንባታ በቅርቡ በአዲስ አበባ ይጀመራል ተብሏል፡፡
ማዕከሉ የህንድ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ለማስተዋወቅ፤ ዘርፉን በማሳደግና ወደ ንግድ በመቀየር የስራ እድል ለመፍጠር እንዲሁም የቴክኖሎጂ የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ ነው፡፡