ንግድን የማሳለጥ መርሐ ግብር የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ በጠ/ሚር ጽ/ቤት እየተካሄደ ነዉ።
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ መዋቅራዊ የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ የግል ዘርፉ ንግድን ለመጀመርና ፋይናንስን በቀላሉ ለማግኘት እንዲችል ምቹ ሁኔታ የመፍጠርን አስፈላጊነት አሥምረውበታል።
በተለይም ጀማሪ ንግዶች ፋይናንስን በቀላሉ ለማግኘት ያሉባቸውን ማነቆዎች ከመፍታት አኳያ የብድር ሥርዓቱን በመከለስ ተንቀሳቃሽ ንብረትን በመያዣነት ለመበደር የሚያስችል አሠራር በሂደት ላይ መሆኑን ጠ/ሚሩ አስታውቀዋል።
ምንጭ፤- ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት