የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ123ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓል ለየት ባለ መልኩ ለማክበር ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ ።
የከተማ አስተዳደሩ የፕሬስ ሴክረታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ እና የባህል የኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊው ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በአሉን ለማክበር ስለተዘጋጁት መርሃግብሮች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በወጣው ፕሮግራም መሰረት ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2011ዓ.ም በብሄራዊ ቤተ- ቤተ መዛግብት የፊልም ፌስቲቫል ይካሄዳል ተብሏል።
ዓርብ የካቲት 22 ቀን 2011ዓ.ም በዓሉን በተመለከተ በጣይቱ ሆቴል የስነ-ጥበብ ድግስ መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የፕረስ ሴክረታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ ጨምረው እንደገለፁት በበዓሉ ዕለት ጠዋት በጊዮርጊስ አደባባይ የተለመደው የዓድዋ ሰማዕታትን የማስታወስ እና የመዘከር ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።
ያንን ተከትሎም በዓሉ ከሚደረግበት የጊዮርጊስ አደባባይ እስከ ዓድዋ ድልድይ የሚደረገው የእግር ጉዞ እና ዓርበኞችን እና የበዓሉ ታዳሚዎችን ግብር የማብላት ስነ-ስርዓትም በቅደም ተከተል እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የበዓሉ ቀን ከሰዓት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ አዘጋጅነት ሁሉም ዜና ያለክፍያ የሚታደምበት የ”አድዋ ፌስቲቫል!” የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚቀርብም ተገልጿል።