Social

በአካል ላይ የሚደርስ ጉዳት መጠንን የሚለካ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የሙከራ ስራ ሊጀምር ነው

በአካል ላይ የሚደርስ ጉዳት መጠንን የሚለካ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የሙከራ ስራ ሊጀምር ነው

ይህ በአደጋም ይሁን በማናቸውም ምክንያት በአካል ላይ የሚደርስ የጉዳት መጠንን የሚለካው  መተግበሪያ ስሪቱ የኢትዮጵያ ሲሆን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት የአካል ጉዳተኝነት መጠን ልኬት በዘልማድ የሚከናወን በመሆኑ በአደጋ ጊዜ በሚከፈል ካሳ መጠን ላይ በፍርድ ቤቶችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አለመግባባቶች ይፈጠሩ ነበር።

ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የደረሰባቸው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ አስልቶ የሚያስቀምጥ መሆኑም ተገልጿል።

ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ገፅ ላይ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ይኸው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተመራማሪዎች ያሰራው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአካል ጉዳተኝነት መጠን መለኪያ መተግበሪያ እና ብሄራዊ መመሪያ የሙከራ ስራ ሊጀምር  ርክክብ ተካሂዷል፡፡

ይህ አዲስ  ቴክኖሎጂ ከተሞከረ በኋላ በሀገሪቱ የህክምና ማዕከላት ወደ ስራ ይገባል ተብሏል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ‹‹ኦርቶፔዲክስና ትራማቶሎጂ›› ማህበር ጋር ወደ ፊት አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በገፁ አስፍሯል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami