EconomyEthiopia

የቻይናው “ሁዋጂያን ግሩፕ”የቴክኖሎጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ከተማ ሊገነባ ነዉ፡፡

የቻይናው “ሁዋጂያን ግሩፕ”የቴክኖሎጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ከተማ ሊገነባ ነዉ፡፡

“ሁዋጂያን ግሩፕ” የሚገነባዉ የኢንዱሰትሪ መንደር  አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ነዉ ተብሏል፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር ከ “ሁዋጂያን ግሩፕ” ፕሬዝዳንት ሁዋሮንግ ዛንግ ከተመራው የተቋሙ አመራሮች ቡድን ጋር በጋራ መስራት በሚቻልበት አካሄድ  ዙርያ መክረዋል፡፡
ምክክሩ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች በሀገር ውስጥ በሚመረቱበትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ለአፍሪካ ገበያ ለማቅረብ በሚቻልበት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር በሚፈጠርበት ሁኔታ እንዲሁም በማምረቻ ተቋማት የሚሰራ የሰው ሀይል ማሰልጠንን የተመለከተ ነዉ፡፡
“ሁዋጂያን ግሩፕ” ካለፉት ሰባት አመት ጀምሮ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ ላይ ያለ ተቋም ሲሆን በአሁኑ ስአት አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለቀላል ኢንዳስትሪ ማምረቻ የሚሆን ና የስራ እድልን የሚፈጥር የኢንዱስትሪ ከተማ ለመገንባት በሂደት ላይ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታው ጀማል ለሁዋጂያን ግሩፕ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀውላቸዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami