EthiopiaTech

በኢትዮጵያ የተጀመረውን የቴክኖሎጂ መነሻ (Tech-Startup) ለመደገፍ ‹‹54 ካፒታል›› የተባለው የግል ኩባንያ 6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ 

በኢትዮጵያ የተጀመረውን የቴክኖሎጂ መነሻ (Tech-Startup) ለመደገፍ ‹‹54 ካፒታል›› የተባለው የግል ኩባንያ 6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
‹‹54 ካፒታል›› በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በመስራት ላይ ሲሆን የምርምር ስራዎች ወደ ምርት፣ አገልግሎትና ሀብት እንዲቀየሩ ለማድረግ፣የቴክኖሎጂ የስራ እድል ፈጠራን ለማበረታታት የመጀመርያውን ዙር የገንዘብ ድጋፍ ነው ያደረገው፡፡
በሰው ሀይል ስልጠና እና በሌሎች ቴክኒካል ጉዳዮችም አገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል፡፡
ድርጅቱ ከኢኖቬሽንና ተክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርሟል፡፡
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሹመቴ ግዛው እና የ‹‹54 ካፒታል›› መስራች ስአድ አወይድ ፈርመውታል፡፡
ዶክተር ሹመቴ የምርምር እና የፈጠራ ስራዎችን ወደ ምርት እና አገልግሎት ለማስገባት እና ወጣቶች ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገ የስራ ፈጠራ ለማበረታታት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የጀመረውን የ2-2-2-2- ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ከዚህ ተቋም መማር አለበት ብለዋል ፡፡
‹‹54 ካፒታል›› በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ የመጀመርያው የግል ተቋም ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami