በኤርትራ ወደ አሰብ ወደብ መዳረሻ ያለው 60 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና ተጠናቀቀ
በኤርትራ ወደ አሰብ ወደብ መዳረሻ ያለው 60 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።
ጥገናው በሁለት ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን፥ ከ121 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል።
የመንገዱ ጥገና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማሳደግ ባለፈ ከዚህ ቀድሞ ተቋርጦ የነበረውን የአሰብ ወደብ የወጪ እና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴ ዳግም ወደ ስራ እንደሚያስገባ ታምኖበታል።
ጥገናው መስመሩን የሚጠቀሙ የጭነት ተሸከርካሪዎችን ክብደት መሸከም እንዲችል ተደርጎ የተሰራ መሆኑም ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እንደገለጸዉ የአዲስ አበባ አሰብ መንገድ 882 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው፥ 811 ኪሎ ሜትሩ በኢትዮጵያ ቀሪው 71 ኪሎ ሜትር ደግሞ በኤርትራ ክልል ውስጥ ይገኛል።