EconomyEthiopia

ከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር  ባላይ  ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ::

ከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር  ባላይ  ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ::
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በወጭ ንግድ አፈፃጸም የሚስተዋሉ ችግሮችን እና የሽያጭ ዋጋ መዛባትን ለመከላካል የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት 1.15 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዷል፡፡

ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚከታተላቸው የግብርና እና አምራች ኢንዱስትሪ ምርቶች 428.919 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲገኝ ማስቻል የወጪ ንግድ ገቢውን ለማሻሻል ከተያዙ ተግባራት ውስጥ አንዱ ነው ሲል በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በግንባታ ላይ ያሉ 5 የሁለተኛ ደረጃ የግብይት ማዕከላትን መከታተል፣ አንድ ማዕከል አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት እና አንድ የቡና መቀበያ ማዕከል መክፈት በሎጂስቲክስ መስኩ የተያዙ እቅዶች ሲሆኑ ፤የኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም ለማሻሻል እና የሀገር ውስጥ ባለሀብት ከውጭ ሀገር ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት የሚሰሩበትን አሰራር ለመፍጠርም መታቀዱ ተገልጿ፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮ-ኤርትራ የጠረፍ ንግድ ስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት ድርድር ማድረግ እንዲሁም በሱማሊያና ሱዳን የጠረፍ ንግድ ጥናት ለማካሄድ በእቅድ የተያዘ ሲሆን ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት የሚደረግ የጫት መጠንና የዋጋ ኮታን በመከለስ ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት እንዲኖር ለማድረግም መታሰቡ ነው የተገለፀው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami