Social

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸዋል

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ 51 ሺህ 229 ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወጥቶላቸዋል

በዕጣ ከተላለፉ ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች በ20/80 ፕሮግራም የተካተቱ ሲሆን ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው።

በዚህም መሰረት በዕጣ ከተላለፉ የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7 ሺህ 127 ባለ ሁለት መኝታ እና 5 ሺህ 455 ቤቶች ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ ናቸው ፡፡

በእነዚህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የተካተቱት በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች ብቻ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ከተማ አስተዳደር ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሃለፊዎች የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ለባለዕድለኞች ተላልፏል፡፡

የከተማ ልማት ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር አባይ  እንደተናገሩት በዚህ በ 13ኛው ዙር የኮንዶሚኒየም ዕጣ የኢንፎርሜሽን  ቴክኖሎጂ፤ ከፀረ ሙስና  ፤ከጀኔራል ኦዲት  እና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በተወጣጡ  ኮሚቴዎች ቴክኖሎጂዎችን በማልማት  እና በማበልፅግ ስራ ላይ እንደተሳተፉ አቶ ተናገረዋል፡፡

 

 

 

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami