ማንችስተር ዩናይትድ እና ፖርቶ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል
ትናንት ምሽት በተደረጉ ሁለት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በመጀመሪያው ዙር የተመዘገቡ ውጤቶች ተቀልብሰዋል፡፡
ፓርክ ደ ፕረንስ ላይ ከፒ.ኤስ.ጂ ጋር የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ በሮሜሉ ሉካኩ ሁለት እና ራሽፈርድ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል 3 ለ 1 ድል አድርጎ፤ በድምር ውጤት 3 ለ 3 አቻ ቢለያይም ዩናይትድ ከሜዳ ውጭ የተሻለ የግብ መጠን ያስመዘገበ በመሆኑ ሩብ ፍፃሜውን ተዋህዷል፡፡
ዩአን ቤርናት ለፓሪሱ ቡድን የማስተዛዘኛዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ፖርቶ በእስታዲዮ ዶ ድራጋዎ ሮማን አስተናግዶ 3 ለ 1 በመርታት ወደ ተከታዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ሱአሬስ፣ ማሬጋ እና ቴሌስ ሲያስቆጥሩ፤ የሪማን ግብ አምበሉ ዴ ሮሲ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አገናኝቷል፡፡
እስካሁን ቶተንሃም.፣ አያክስ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ፖርቶ ሩብ ፍፃሜውን ተዋህደዋል፡፡
ቀጣይ ሳምንት ቀሪዎቹ አራት ቡድኖች የሚለዩ ሲሆን ማክሰኞ ዩቬንቱስ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ማንችስተር ሲቲ ከ ሻልከ 04 እንዲሁም ዕረቡ ባርሴሎና ከ ሊዮን እና ባየርን ሙኒክ ከ ሊቨርፑል ይጫወታሉ፡፡