የገቢዎች ሚኒስቴር ደረሰኝ ባልቆረጡ ስምንት ትላልቅ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ ወስጄያለሁ አለ፡፡
በሚኒስቴሩ የታክስ ማጭበርበርና ምርመራ ዳይሮክትሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ
እንደተናገሩት በሳምንቱ ዉስጥ በ8 ትላልቅ ድርጅቶች ላይ ኦፕሬሽን ተደርጎ ስምንቱም ደረሰኝ ሳይቆርጡ በመገኘታቸዉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸዉን ተናግረዋል፡፡
ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ 14 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ ከስምንቱ ድርጅቶችም 5ቱ መርካቶ አከባቢ የሚገኙ አከፋፋይና ጅምላ ሻጭ ነጋዴዎች ናቸዉ ፡፡
በቀጣይም ደረሰኝ በማይቆርጡ ነጋዴዎች ላይ የሚደረገዉ ቁጥጥር በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል ብለዋል ዳይሬክተሩ ፡፡
አቶ ሲሳይ ህብረተሰቡ እስካሁን ያደረገውን ትብብር በማመስገን ከዚህ በኋለም የተለመደውን ትብብሩን ይቀጥልበት ዘንድ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡