በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከሰተ ያለውን የትራፊክ አደጋ በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት ሊካሄድ ነው፡፡
ጥናቱ የአዲስ አዳማ የክፍያ መንገድን ጨምሮ በአገሪቷ ባሉ በተመረጡ 2000 ኪሜ መንገዶች ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
ጥናቱን ለማካሄድ የትራንስፖርት ሚንስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ጥናቱን ከሚያካሂደው EPTISA service deingeniera s.c ከተባለ አለም አቀፍ የስፔን ድረጅት ጋር ተፈራርመዋል ፡፡
ለጥናቱ የሚደረገው ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
የህዝቡን የትራፊክ ደህንነት ትርጉም ባለው መልኩ በቀጣይ ይቀርፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ጥናተ ከሚያካትታቸው ስራዎች ውስጥ የመንገድ ዲዛይን፣ግንባታ ፣ ጥገና እና የመንገድ ሀብት ማስተዳደር ለአደጋ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ ጉድለቶችን ስለመኖራቸው እንዲሁም ከአሽከከርካሪ መንጃ ፍቃድ አሰጣጥ እና ከተሸከርካሪ ደረጃዎችና አይነቶች ጋር ያሉ ክፍተቶች ላይ ያተኩራል፡፡
ከኢትዮጵያ መንገዶቸ ባለስልጣን እንዳገኘነዉ መረጃ የጥናቱ መካሄድ አሳሳቢ እየሆነ ለመጣው የትራፊክ አደጋ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትያስችላል ተብሏል፡፡