የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የብሄራዊ የሃዘን እንዲሆነ አወጀ፡፡
ምክር ቤቱ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሐገር ዜጎች ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም የአንድ ቀን ብሄራዊ የሐዘን ቀን እንዲታወጅ በሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001/ በአዋጅ ቁጥር 863/2006 እንደተሻሻለ አንቀጽ 22 ንዑስ አንቀጽ (2) መሰረት መወሰኑን አስታውቋል።
ስለሆነም የሪፐብሊኩ ሰንደቅ አላማ መጋቢት 2 ቀን 2011 በመላው የአገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች እና በውጭ ሐገር በሚገኙ ኤምባሲዋች የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ዝቅ ብሎ የሚውለበለብ ይሆናል ብሏል።
ምክር ቤቱ ብሄራዊ የሀዘን ቀኑን ያወጀው ትላንት ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተክትሎ ነው፡፡