የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዉሮፕላን አደጋዉ የሞቱትን ሰዎች የመለየቱ ስራ አስከ አምስት ቀን ሊፈጅብኝ ይችላል አለ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አስራት በጋሻዉ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የሟቾቹን ማንነት ሙሉ ለሙሉ ለማወቅ ቢየንስ እስከ አምስት ቀን ሊቆዩ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ትላንት በቢሾፍቱ አካባቢ በደረሰዉ የአዉሮፕላን አደጋ የ35 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ ይታወቀል፡፡