Ethiopia

የአውሮፕላን አደጋ መንስኤውን የሚመረምር ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ ጀመረ

የአውሮፕላን አደጋ መንስኤውን የሚመረምር ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ ጀመረ

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እሁድ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ የመከስከስ አደጋ ያጋጠመውንና ለ157 ሰዎች ሕልፈት ምክንያት የሆነውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የአደጋ መንስኤ የሚያጣራ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ስራ ገብቷል።

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ የአውሮፕላን አደጋ መንስኤውን የሚመረምር ኮሚቴ አዋቅሮ ስራ ጀምሯል ነው የተባለው።

ኮሚቲው የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ሂደቱ ከሚሳተፉ አባላት ውስጥ የአሜሪካ ብሄራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ  የምርመራ ቡድን አባላት አዲስ አበባ ገብተዋል ተብሏል።

ዘገባው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami