በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ስምምነቶች ተደረጉ
ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል በርካታ ስምምነቶች መደረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሰምተናል ፡፡
በኢትዮጵያ በኩል የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ሥልጠና የዐቅም ግንባታና ስትራቴጃዊ የልምድ ልውውጥን የሚያካትተውን የመከላከያ ትብብር ስምምነት እንደፈረሙ ታውቋል::
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በበኩላቸው የፈረንሳይ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን በስራ ላይ የሚያውሉበትን ጉዳይ የተመለከተ የመግባቢያ ሰነድ ለምጣኔ ሀብት ማሻሻያ የፋይናንስ ትብብር የጋራ መግባቢያና እና የቅርስ ትብብርን በተመለከተ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን መፈራረማቸው ታውቋል::
የእነዚህ ስምምነቶች መፈረም በኢትዮጵያ እና በፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከሩን ማሳያ ነው ተብሎለታል:፡