EthiopiaSportSports

አርሰናል የደረሰበትን የመጀመሪያ ሽንፈት ቀልብሶ የሩብ ፍፃሜውን ተዋህዷል

በርካታ የዬሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተካሂደዋል፡፡

ከሜዳው ውጭ የ3 ለ 1 ሽንፈት ገጥሞት የተመለሰው አርሰናል ኤመሬትስ ላይ የፈረንሳዩን ሬን 3 ለ 0 ሲረታ፤ በድምር ውጤት 4 ለ 3 ድል አድርጎ ወደ ሩብ ፍፃሜው መሻገር ችሏል፡፡

ጋቦናዊው ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በምሽቱ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር፤ ለወጣቱ ሜትላንድ ኒልስ ጎል አመቻችቶ አቀብሏል፡፡ ኦባማያንግ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል፡፡

ወደ ዩክሬን ያመራው የእንግሊዙ ቼልሲ ዳይናሞ ኬቭን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ፤ በአጠቃላይ ውጤት የ8 ለ 0 የበላይነት ተከታዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

ሰማያዊዎቹ በግብ ሲንበሻበሹ ፈረንሳያዊው ኦሊቪዬ ጅሩ ሶስት በማበርከት ሀትሪክ ሰርቷል፤ ማርኮስ አሎንሶ እና ወጣቱ ካሉም ሁድሰን- ኦዶይ ቀሪዎቹን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

በምሽቱ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች የጣሊያኑ ናፖሊ በኦስትሪያው አር. ቢ ሳልዝበርግ 3 ለ 1 ቢሸነፍም በደርሶ መልሱ 4 ለ 3 በመርታት ስምንቱን ቡድኖች ተቀላቅሏል፡፡ ክራስኖዳር 1 ለ 1 ቫሌንሲያ በድምር ውጤት (2 ለ 3) ፤ ቤንፊካ 3 ለ 0 ዲናሞ ዛግሬብ (3 ለ 1) ፤ ኢንተር ሚላን 0 ለ 1 አይንትራክት ፍራንክፉርት (0 ለ 3) ፤ ስላቪያ ፕራሃ 4 ለ 3 ሲቪያ (6 ለ 5) ፤ ቪያሪያል 2 ለ 1 ዜኒት ፒተርስበርግ (5 ለ 2) ፡፡

በአጠቃላይ አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ናፖሊ፣ ቤንፊካ፣ ቪያሪያል፣ ቫሌንሲያ፣ አይንትራክት ፍራንክፉርት፣ ስላቪያ ፕራሃ ሩብ ፍፃሜውን የተዋሀዱ ቡድኖች ናቸው፡፡

የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል ከከስዓት በኋላ ይፋ ይሆናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami