Economy

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ።

 

በቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ በሃገሪቱ በተካሄደ ዓለም ዓቀፍ ልዩ የቡና ትርኢት ቀርቧል።

 

ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ይኸው አውደትርዒቱ ከመጋቢት 2 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቻይና ፑኤር ከተማ ተካሂዷል። እንደ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት  ገለፃ በትርዒቱ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ቡና  ልዩ ጣዕምና ጥራት እንዲሁም ብዝሃነት  ለቻይና ህዝብ አስታዋውቃበታለች።

ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ በቻይና ገበያ ተመራጭ መሆኑና በቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እያደገ መምጣቱም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

 

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጥሬ ቡና የሚልኩ አገራት እሴት በመጨመር ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስቸሉበት ልምድም በአውደትርዒቱ ቀርቧል።

ከትርኢቱ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ልዑክ ከፑኤር ከተማ ከፍተኛ ሃላፊዎችና የዩና ግዛት ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ቢሮ ተወካዮች ጋር በዘርፉ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ቡና በማቀነባበር፣ በማልማት፣ በማምረት፣ በመሸጥና ተያያዥ ዘርፎች የተሰማሩ ከአንድ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami