Uncategorized

በሞዛምቢክ በተከተሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡

በሞዛምቢክ በተከተሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ፊሊፔ ኒዩሲ አደጋው የከፋበቸውን አከባቢዎች ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት ከሁኔታው አንጻር የሟቾች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

በቢሲ እንደዘገበው ቤራ በተሰኘችው የወደብ ከተማ አቅራቢያ የተነሳውና በሰዓት 177 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘገው አውሎ ንፋስ የግማሽ ሚሊዮን ነዋሪዎችን መኖሪያ ቤት አውድሟል፡፡

አደጋውን ተከትሎም በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች የወደሙ ሲሆን  የመብራት እና  የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ  ተቋርጧል ፡፡

ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በወጀብ የታጀበው አውሎ ንፋስ  በደቡባዊ አፍሪካ ሃገራት ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል፡፡

እስካሁንም በዚምባቡዌ 98 ሰዎች ሲሞቱ 217 ሰዎች ደግሞ የገቡበት አልታወቀም፡፡

በተጨማሪም በማላዊ 122 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡

 

አብነት ታምራት

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami