AfricaEconomy

ዋሽንግተን በግብጽ መከላከያ ተቋም ተቆጥታለች፡፡

ዋሽንግተን በግብጽ መከላከያ ተቋም ተቆጥታለች፡፡

የግብፅ መከላከያ ሀይል በሀገሪቱ ባሉት የኢኮኖሚ ተቋማት የበዛ ጣልቃ ገብነት አለው የሚሉ የሪፓብሊካን እና የዲሞክራት ፓርቲ አባላት በሁኔታው ቅር መሰኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የዲፕሎማቲክ መንጮች ተናገሩ ብሎ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የፓርቲ አባላቱ የግብፅ መከላከያ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ስለተቆጣጠረ የውጭ ኢንቨስተሮች ለኪሳራ እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡

ግብፅ ውስጥ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመከላከያ ሚኒስቴር በራሱ ቁጥጥር ስር ስላደረጋቸው የአሜሪካን ጨምሮ  በርካታ የምእራባዊያን ኢንቨስተሮች በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ከአሁን ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው ሪፖርት የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት  ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አጀንዳዎቹን እንደገና መፈተሸ አለበት የሚል ሀሳብ አንፀባርቋል፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)  በግብፅ የግሉ ዘርፍ በመዳከሙ እና የመከላከያው ጣልቃ ገብነት በማየሉ ስራ አጥነት እና የኢኮኖሚ እድገር ማሽቆልቆል እየተስፋፋ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡

በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተደጋጋሚ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን ሲተቹ ይደመጣሉ ምን እንኳን ሰሚ ባያገኙም ይላል ዘገባው፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami