AfricaSportSports

ግብፃዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ሚዶ ለእስር ሊዳረግ ነው ተባለ

የቀድሞው ግብፃዊው እግር ኳስ ተጫዋች አህመድ ሆሳም ሁሴን (ሚዶ) በአንድ ዓመት እስር ወይኒ ሊወርድ እንደሚችል የሳውዲ ብዙሃን መገናኛዎችን ዋቢ አድርጎ ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡

የቀድሞው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ሚዶ በትናንትናው ዕለት አንድ የአል- ዌህዳ ደጋፊን በቲዊተር ገፁ ተሳድቧለ ተብሎ ክስ ከቀረበበት በኋላ ከሳውዲ አረቢያው አል- ዌህዳ እግር ኳስ ቡድን ስንብት ደርሶታል፡፡

ሆሳም በቅርቡ ከአንድ የክለቡ ደጋፊ ጋር በቲዊተር ገፅ ላይ ግበረ ገብነት የጎደላቸው ቃላትን በመጠቀም ተንኳሽ መልዕክት መመላለሱ ተነግሯል፡፡

‹‹የአል- ዋሄባ ክለብ ቦርድ የግብፃዊውን የቀድሞ ተጫዋች አህመድ ሆሳም (ሚዶ) ስንብት ላይ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡ ክለቡም ከቡድኑ ጋር ለነበረው ቆይታ ያመሰግናል›› የሚል መልዕክት የክለቡ ይፋዊ የቲውተር ገፅ ላይ ሰፍሯል፡፡

የ36 ዓመቱ የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች እና አሰልጣኝ የቀረበበትን ክስ በማጣጣል የቲውተር ገፁ እንደተጠለፈበትም አስተባብሏል፡፡

ከስንብቱ በኋላ ከክለቡ ጋር ለነበረው ቆይታ ለአል- ዌህዳ ክለብ እና ደጋፊዎች ምስጋናውን አድርሷል፡፡

በሳውዲ ህግ መሰረት አንድ ግለሰብ ስማርት ስልኮችን በመጠቀም የሌላኛውን ሰው የግል ህይወት የሚጎዳ ወይንም የስድብ መልዕክት ቢያስተላልፍ የአንድ ዓመት እስር እና የ500 ሺ የሳውዲ ሪያል ይቀጣል፤ አሊያ ከሁለት አንዱ ቅጣት ይተላለፍበታል ይላል፡፡

ሚዶ የአል- ዌህባ ክለብ የቴክኒክ ኃላፊ በመሆን ከተሾመ በኋላ፤ ቡድኑ 13 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን በስድስቱ ድል ሲቀናው፣ በአራቱ ተሸንፎ በሶስቱ ነጥብ ተጋርቷል፡፡

ሚዶን ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ባለፈ በተጫዋችነት ዛማሊክ፣ ማርሴ፣ ሮማ፣ ቶተንሃም፣ ሚድልስብራ እና በሌሎች በርካታ ክለቦች ያሳለፈ ሲሆን በአሰልጣኝነት ዛማሊክ፣ ኢስማይሊ፣ ዋዲ ዴግላ መምራት ችሏል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami