AfricaDisaster

በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለተጎጅዎች የሚሆን የውጭ እርዳታ መግባት ጀምሯል፡፡

በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለተጎጅዎች የሚሆን የውጭ እርዳታ መግባት ጀምሯል፡፡

በሞዛምቢክ፣ ማላዊ እና ዚምባቡዌ ከባድ አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ቁጥራቸው 3 መቶ የሚደርሱት ሲሞቱ ከ2.6 በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአደጋው ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች የእለት ደራሽ እርዳታ እንዲደረግላቸው በጠየቀው መሰረት የተለያዩ ሀገራት ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የመንግስታቱ ድርጅት ለተጎጂዎቹ 20 ሚሊዮን ዶላር በመለገስ ድጋፉን ከራሱ ጀምሯል፡፡

የአውሮፓ ህብረትም 3.9 ሚሊዮን ዶላር በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች አንዲሰጥለት ፈቅዷል ነው የተባለው፡፡ የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ የ350 ሺህ ዶላር ድጋፍ ሰጥቷል፡፡

ከዓለም እና አህጉር አቀፍ ተቋማቱ በተጨማሪ ሀገራት በተናጠል ለአደጋው ተጋላጮች የእርዳታ እጃቸውን እየዘረጉ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡

እንግሊዝ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለመርዳት ቃል ስትገባ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች 4.9 ዶላር ለመስጠት ማሰቧን ኤሜሬትስ የዜና ወኪል በዘገባው አስነብቧል፡፡

የጎረቤት ታንዛንያ መከላከያ ተቋም ደግሞ 238 ቶን ምግብ እና መድሃኒት ለተፈናቃዮቹ እንዲጓጓዝ አድርጓል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami