ጥረት ኮርፖሬት ዓመታዊ ትርፉ ከእቅድ በታች መሆኑን አስታወቀ::
ኮርፖሬቱ በፈረንጆቹ 2018 በጀት ዓመት 189 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን በሪፖርቱ ፍፋ አድርጓል፡፡
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 709 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም የእቅዱን 26 በመቶ ብቻ ማሳካቱን ነው የገለፀው፡፡
ተቋሙ ያለፈውን ዓመት የስራ እንቅስቃሴውን በባህርዳር በመገምገም ላይ ሲሆን ካለፈው በጀት ዓመት አንፃር ሲታይ የ44 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡
ይሁን እንጂ ኮርፖሬቱ በስሩ ካሉት ኩባንያዎች አምስቱ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደገጠማቸው በመድረኩ ላይ ተነግሯል፡፡
ጥረት ኮርፖሬት በስሩ 19 ኩባንያዎችን አቅፎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በቅርቡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወደ ክልሉ የህዝብ ሀብትነት እንዲሸጋገር መወሰኑ ይታወቃል፡፡
ዘገባው የኢቢሲ ነው፡፡