ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የክበበ ጸሀይ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን እየጎበኙ ነው
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የክበበ ጸሀይ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን እየጎበኙ መሆናቸውን የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቋል፡፡
ማዕከሉ በ1956 የተመሰረተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 200 የሚደርሱ ወላጅ አልባ እና አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ተቀብሎ በመንከባከብ ላይ ይገኛል።
ክበበ ጸሀይ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ህፃናትን ዘጠኝ አመት እስኪሞላቸው ድረስ እንደሚያሳድግና ከዘጠኝ አመታቸው በኋላ ወደ ሌሎች ማዕከላት እንደሚልክ ተነግሯል፡፡
ክበበ ጸሀይ አሁን ያለበት ቦታ ከአንጋፋዉ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የተበረከተ መኖሪያ ቤታቸዉ ነበር ፡፡