የሁዋን ጓይዶ ባለቤት በዋይት ሀውስ በእንግድነት ተጋበዙ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ራሳቸውን የቬንዙዌላ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው የሾሙትን የሁዋን ጓይዶን ባለቤት በነጩ ቤተ መንግስት ተቀብለው አነጋገረዋቸዋል፡፡
የጓይዶ ባለቤት ፋቢና ሮዛሌስ የባለቤቴ ደህንነት አደጋ ላይ ነው እና የርስዎን እርዳታ እሻለሁ ሲሉ ትራምፕን ተማፅነዋል፡፡
ትራምፕም በበኩላቸው እሱን ለእኛ ተውት እኛ ከጎናችሁ ስለመሆናችን ቅንጣት ጥርጣሬ አድንዳይገባዎ በማለት ቃላቸውን ሰጥተዋቸዋል፡፡
አሜሪካ እና ሩሲያ በቬንዙዌላ ጉዳይ አንዱ ማደዱሮን ሌላው ጓይዶን ደግፈው የፖለቲካ ንትርክ ውስጥ ከገቡ ሰነባብተዋል፡፡
ሩሲያ ጦሯን ከቬንዙዌላ በፍጥነት እንድታስወጣ መስጠንቀቂያ የሰጡት ትራምፕ ይህ ካለሆነ ግን ሁሉም አማራጮች እጃቸው ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ከክሬምሊን ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን የምትነግረን ዋሽንግተን አለመሆኗን ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተረዱት አይመስልም የሚል መግለጫ ተሰምቷል፡፡
የአሜሪካው የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን በቱይተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እኛ ለተቸገሩት ቬንዙዌላዊያን ሰብዓዊ እርዳታ ስልክ ሩሲያ ወታደሮቿን ከቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ጋር ልካለች ሲሉ ሞስኮን ወቅሰዋል፡፡
ትራምፕ ደግሞ የቬንዙዊያውን ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን የኩባ አሻንጉሊት ነው ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡
ከሩሲያ በኩል በአንዲት ሉዓላዊት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባ ከመንግስት ግልበጣ ተለይቶ አይታይም የሚል አቋም አለ፡፡
መንገሻ ዓለሙ