EthiopiaSocial

በአዲስ አበባ 3 ሺህ 147 የጎዳና ላይ ነዋሪዎች ከጎዳና ተነስተዋል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ 3 ሺህ 147 የጎዳና ላይ ነዋሪዎች ከጎዳና ተነስተዋል ተባለ፡፡

 ጎዳና ላይ ከነበሩት 701  ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ቀሪዎቹን ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህ የተገለጸዉ ለአዲስ አበባ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃግብር በተካሄደ በት ወቅት ነዉ፡፡

የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተመሠረተው የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ባደረገው ጥረት የጎዳና ላይ ነዋሪዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል በእስከ አሁን በማገገሚያ ቆይታቸው የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እና የስነልቦና ትምህርቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡

ለዚህ ስራ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የተገኙት ከንቲባ ታከለ ኡማ እስከአሁን ማገገሚያ የገቡትን ስራ የማስጀመርና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቅርቡም ተጨማሪ የጎዳና ላይ ልጆችን የማንሳትና ወደ ማገገሚያ ማዕከል የማስገባት ስራው እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ለማህበራዊ ትረስት ፈንዱ በዋናነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን፤ የከተማ አስተዳደሩ የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ህብረተሰቡን እና ተቋማትን በማስተባበር የሚያደርገውን ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami