EconomyEthiopia

ቦይንግ ከኢትዮጵያ አየር መንገዱ አደጋ ጋር በተያያዘ እየተከሰሰ ነው

ቦይንግ ከኢትዮጵያ አየር መንገዱ አደጋ ጋር በተያያዘ እየተከሰሰ ነው

በኢትዮጵያ አየር መንገዱ አደጋ ህይወቱን ያጣ አንድ ግለሰብ ቤተሰቦች በአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ቦይንግ ላይ በአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት ክስ መመስረታቸው ተሰምቷል።

በአደጋው ህይወቱ ያለፈው ጃክሰን ሙሶኒ የሚባል ሩዋንዳዊ ግለሰብ ዘመዶች ናቸው በቦይንግ ላይ ክሱን የመሰረቱት፡፡

የግለሰቡ ቤተሰቦች በክሳቸው ላይ አደጋው የደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ ኤት አውሮፕላን በአውቶማቲክ የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓቱ ላይ የዲዛይን ችግር አለበት ሲሉ አመልክተዋል።

ከአምስት ወራት በፊት ከተከሰከሰው ተመሳሳይ የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን በኋላ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ አደጋው ሲደገም ቦይንግ 737 ማክስ የተባለው አይነት ስሪት ያላቸው አውሮፕላኖች በሙሉ ከበረራ ታግደዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩት 157 መንገደኞች በሙሉ በአዳጋው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ በቀረበበት ክስ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

ረቡዕ እለት ቦይንግ ከአደጋዎቹ ጋር ግንኙነት አለው የተባለው በአውሮፕላኑ መቆጣጠሪያ ላይ ያለው ችግር መፍትሄ እንደተበጀለት እና የሶፍትዌር ማሻሻያ እንዳደረገ ይታወሳል ።

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami