ለሀገራችን ኢንዱስትሪ ውጤታማነት በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ተቀናጅቶ መፍታት ይገባል ተባለ
ለሀገራችን ኢንዱስሪ ውጤማነት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎቸ ያሉባቸውን ችግሮች ተቀናጅቶ መፍታት ይገባሉ ሲሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ተናገሩ
ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት ከፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ስትሪንግ ኮሚቴ ጋር በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
ስትሪንግ ኮሚቴው አነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ ባደረጓቸው ችግሮች፣በዘርፉ በተሰሩ ስራዎችና ያሉ ችግሮች እንዲሁም በመፍትሄ አምጪ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡
የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን ውጤት እንዳላመጣ የተገመገመ ሲሆን ለዚህም የዳረጉት የአደረጃጀት፣የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽ፣ የፋይናንስ አጠቃቀም እና የሼዶች በአግባቡ ስራ ላይ አለመዋል መሆናቸው በውይይቱ ተጠቅሰዋል፡፡
ወ/ሮ ፈትለወርቅ ችግሮቹን ለመፍታት ዘርፉን ለመደገፍ የተቋቋሙ ተቋማት፣ ክልሎች እና ድርሻ ያላቸው ድርጅቶች ተቀናጅው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡
በፌዴራል ደረጃ የሚደረገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሎች ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ሊያሰራቸው የሚችለውን አደረጃጀት በመፍጠር ከባለድርሻዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት ይኖርባቸዋል ያሉት ሚኒስትሯ በካፒታል እቃዎች ግዥ መጓተት አምራቾችን ከሚደርስባችው አላስፈላጊ ወጪ ለመታደግ እና የውጪ ምንዛሪ ችግርንም ለማቃለል በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ማሽኖችንና ግብዓቶችን በመጠቀም ከውጪ የምናስገባቸውን ማሽኖችን መጠን መቀነስ ይገባልም ብለዋል፡፡