PoliticsWorld News

ሁዋን ጓይዶ ያለመከሰስ መብታቸውን ተነጠቁ፡፡

ሁዋን ጓይዶ ያለመከሰስ መብታቸውን ተነጠቁ፡፡

የቬንዙዌላ ምክር ቤት ራሳቸውን የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው የሾሙትን  ሁዋን ጓይዶን ን ያለመከሰስ መብት በማንሳት ለክስ አዘጋጅቷቸዋል ተብሏል፡፡

ፓርላማው ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጓይዶ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ እና ሰውየው አጠፉ በተባለው ልክ እንዲጠየቁ ባቀረበው ሀሳብ ነው፡፡

የፓርላማውን ውሳኔ ተከትሎ አቃቤ ህግ ጓይዶን መምርመር እና ለሀገሪቱ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ነው የተባለው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ጓይዶ በቬንዙዌላ ፍርድ ቤት በሁለት ወንጀሎች እንደሚፈለጉ አመላካች ሁኔታዎች አሉ፡፡

አንደኛው በሀገሪቱ በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ማግስት በሚመሩት ምክር ቤት ራሳቸውን ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት አድርገው መሾማቸው ነው፡፡

ሁለተኛው ሊያስከስሳቸው ይችላል የተባለው ጉዳይ ደግሞ የተጣለባቸውን የውጭ ሀገር የጉዞ እገዳ በመጣስ ወደ  ደቡብ አሜሪካ ሀገራት ያደረጉት የጉብኝት ጉዞ ነው፡፡

ጓይዶ ግን የመጣው ይምጣ እንጂ የማዱሮን የሀይል አገዛዝ ለመጣል የማደርገውን እንቅስቃሴ የሚያስቆመኝ አካል የለም እያሉ ነው፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami