AfricaSocial

ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያን ልትጎበኝ ነው፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያን ልትጎበኝ ነው፡፡
ኢቫንካ በአይቮሪኮስት በሚካሄደው የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ በሚያተኩረው ስብሰባ የምትካፈል ሲሆን ቀጣይ የጉብኝት መዳረሻዋ ኢትዮጵያ ናት፡፡
ኢቫንካ በሁለቱም ሀገራት ቆይታዋ ከኢትዮጵያ እና ከአይቮሪኮስት ሴት ስራ ፈጣሪዎች እና ፖለቲከኞች ጋር ውይይት ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አባቷ የሚመሩት ዋይት ሀውስ አማካሪ የሆነቸው ኢቫንካ የዚህ ወር የአፍሪካ ጉብኝቷ ዋና ዓላማ በበላይነት የምትመራውን ግሎባል ውመንስ ኢምፓወርመንት ኢኒሼቲቭ ለማስተዋወቅ ነው፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኢኒሼቲቩ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር እስከ 2025 አፍሪካን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የሚኖሩ 50 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዷል፡፡
የእናቷ የቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የአፍሪካ ህፃናትን የማገዝ ዓላማ የነበረው ጉብኝት ኢቫንካ ይህን ጎዞ እንድታደርግ እንደገፋፋት ተነግሯል፡፡
ይሁን እንጂ የፖለቲካ አዋቂዎች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሁን ቀደም የአፍሪካ ሀገራት ላይ የስድብ ንግግር ማድረጋቸው በእናት እና ልጅ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት ይፈጥራል የሚል ስጋት አላቸው፡፡
መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami