በአሰልጣኝ ሰላም ዘራይ የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን ፤ በ2020 ለሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድር ሴቶች እግር ኳስ የመጀመሪያ ዙር የመልስ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በማቅናት ትናንት ከከሰአት በፊት ደርሷል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ በአዲስ አበባ ስታዲየም የዩጋንዳ አቻውን ከቀናት በፊት ዕረቡ ዕለት 3 ለ 2 መርታቱ ይታወሳል፡፡
ቡድኑ እስከ የጨዋታው መደበኛ ክፍለጊዜ መጠናቀቂያ ድረስ 3 ለ 0 ሲመራ የነበር ቢሆንም ባለቀ ጊዜ በተቆጠሩበት ሁለት ግብ ወደ ቀጣ ዙር የማለፍ ዕደሉን ጥርጣሬ ውስጥ ከትቶታል፡፡
የመልስ ግጥሚያው ነገ ከሰዓት በኋላ በፊሊፕ ኦሞንዲ ስታዲየም የሚከናወን ሲሆን ኢትዮጵያ ውጤቷን አስጠብቃ የምትወጣ ከሆነ በሁለተኛው ዙር ከካሜሮን ጋር የምትገናኝ ይሆናል፡፡