የ2018/19 የኤፍ ኤ ኤመሬትስ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት፤ ቡድኖች ወደ ፍፃሜ ዋንጫ ለማለፍ እያለሙ ይጫወታሉ፡፡
በነገው ዕለት የአራትዮሽ ዋንጫ ግስጋሴው ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ጋር በግዙፉ ዌምብሌይ ይጫወታል፡፡
ከአራቱ ዋንጫዎች የካራባዎ ዋንጫ ጉዞን በድል የፈፀመው የፔፕ ጓርዲዮላው ቡድን፤ ከክሪስ ሁተኑ ክለብ በኩል ጠንከር ያለ አጨዋወት ሊጠብቀው እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
ፔፕ ወጣት ተጫዋቾችን ልምድ ካላቸው ጋር አዋህዶ ሊያሰልፍ እንደሚችል ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በሩብ ፍፃሜው ሲቲ ሰዋንሲን 3 ለ 2 በማሸነፍ ለዚህ ዙር ሲበቃ፤ ብራይተን እና ሚልወል ሙሉ ጨዋታውን በሁለት አቻ ውጤት አጠናቅቀው፤ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት 5 ለ 4 ድል በማድረግ ነው፡፡
ይህ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1፡30 ይደረጋል፡፡
በበነጋታው እሁድ ደግሞ ሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ በዋትፎርድ እና ወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ መካከል ይከናወናል፡፡
ማንችስተር ዩናይድን ከውድድሩ አሰናብቶ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለው የኑኖ እስፕሪቶው ቡድን ወልቭስ ለዋንጫው የማለፍ ዕድል ተሰጥቶታል፡፡
አሸናፊዎቹ ቡድኖች ለፍፃሜ ጨዋታ የሚበቁ ይሆናል፡፡