ኤርትራ በሱዳን የሚኖሩ ዜጎቿን አሰጠነቀቀች፡፡
ካርቱም የሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲ በፃፈው ደብዳቤ በተለይ በካርቱም እና አካባቢዋ የሚኖሩ ወይም ለስራ ጉዳይ ወደ ስፍራው የተጓዙ ኤርትራዊያን በሚንቀሳቀሱበት ወቅት አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ በመያዝ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የኤርትራ መንግስት በሱዳን ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን በመገንዘብ ነው ይህን ደብዳቤ የፃፈው፡፡
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በካርቱም በመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ለተቃውሞ እንደወጡ ተመልሰው አልገቡም ተብሏል፡፡
አሁን ላይ በሱዳን በመከላከያ እና የደህንት ሰዎች መካል መጠነኛ አለመግባባት ተፈጥሯል የሚል ወሬ መሰማቱን ተከትሎ በሀገሪቱ ከቀድሞው የበለጠ ውጥረት ሰፍኗል፡፡
የዓይን እማኞች እንደሚሉት ከሆነ የደህንነት አበላት ሰልፈኞችን ለመበተን ሀይል ሲጠቀሙ መከላከያው ጣልቃ የመግባት አዝማሚያ አሳይቷል፡፡
መንገሻ ዓለሙ